የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የሚሰጡ ድጋፎች

የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የሚሰጡ ድጋፎች

በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ይከታተላሉ።   በህይወት ዘመናችን ውስጥ 20% የምንሆነው፣ ወይም ከእያንዳንዱ 5 ሰው 1ዱ፣ የተወሰነ የአካል ጉዳት ሊገጥመው ይችላል።

ሁሉም አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እኩል የትምህርት እድል፣ እና ከአድሎ ነጻ የመሆን መብት አላችው።በተማሪዎቹ የአካል ጉዳት ተፈጥሮ እና በትምህርታቸው በሚያደርሰው ተጽዕኖ ላይ በመመስረት፣ ተማሪዎች እኩል ተደራሽነት እንዲያኙ እና በትምህርት እንዲሳተፉ ትምህርት ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ እርዳታዎች፣ ማሻሻያዎች፣ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ መመሪያ፣ ወይም ሌሎች ድጋፎችን መስጠት ሊያስፈልገው ይችላል።

  • በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ መመሪያ የሚያስፈልጋቸው አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች “ልዩ ትምህርት” በ “Individualized Education Program (IEP፣ የግለሰብ የትምህርት ፕሮግራም) በኩል መቀበል ይችላሉ።
  • መጠለያ የሚያስፈልጋቸው አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች “Section 504 Plan (የአንቀፅ 504 እቅድ)” ሊኖራቸው ይችላል። 

ተማሪው የአካል ጉዳተኛ እንደሆነ እና የተስተካከለ ወይም ልዩ መመሪያ እንደሚያስፈልገው ካሰቡ፣ የትምህርት ቤቱን ዲስትሪክት ግምገማ እንዲያደርግ መጠየቅ ይችላሉ።

ስለ IEPዎች፣ የአንቀፅ 504 እቅዶች፣ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ግምገማዎች እና ጥበቃዎች እዚህ የበለጠ ይወቁ፦

Find additional resources here:

Supports at School

Disability Identity

Accessibility