በትምህርት ቤቶች የሚፈጸም አድልዎን መፍታት
አድልዎ በአንድ ሰው ላይ ጥበቃ የሚደረግለት ምድብ ተብሎ የሚጠቀሰው ቡድን አባል በመሆኑ ምክንያት የሚፈጸም ኢ-ፍትሀዊ ወይም እኩል ያልሆነ አያያዝ ወይም ትንኮሳ ነው። A ጥበቃ የሚደረግለት ምድብ የጋራ ባህሪያትን የሚጋሩ እና በሕጉ ከአድልዎና ትንኮሳ ጥበቃ የሚደረግላቸውን ሰዎች ይይዛል።1
በዋሽንግተን ግዛት ሕግ ጥበቃ የሚደረግላቸው ምድቦች የሚከተሉት ናቸው:
• ዘር እና ቀለም
• ብሔራዊ ማንነት
• ሀይማኖት እና እምነት
• ጾታ
• የጾታ ማንነት
• የጾታ መገለጫ
• የጾታ ገጽታ
• የዘማችነት ወይም ውትድርና ደረጃ
• አካል ጉዳተኝነት
• የእንስሳትን አገልግሎት መጠቀም
አድሏዊ ትንኮሳ:
ጥበቃ የሚደረግለትን ምድብ መሰረት አድርጎ የሚፈጸም +
አደገኛ አካባቢ ለመፍጠር በቂ የሆነ ነው
አድሏዊ ትንኮሳ የግድ የተወሰነን ሰው ዒላማ አድርጎ የማይፈጸም ሲሆን
የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል:
• ማስፈራሪያዎች
• ስም ማውጣት
• ክብርን የሚነኩ ቀልዶች
• አካላዊ ጥቃት
• አካልን የሚፈታተን፣ የሚጎዳ ወይም
የሚያዋርድ ሌላ ባህሪ2
አደገኛ አካባቢ አድሏዊ ትንኮሳ በአንድ ተማሪ የመሳተፍ ወይም ትምህርት ቤቱ ወይም ዲስትሪክቱ ከሚያቀርባቸው አገልግሎቶች፣ ተግባሮች ወይም እድሎች ተጠቃሚ የመሆን ችሎታ ላይ በበቂ ሁኔታ ጣልቃ በሚገባበት ደረጃ ከባድ ሲሆን፣ ዘልቆ ሲገባ ወይም ቀጣይነት ሲኖረው ይፈጠራል። አደገኛ አካባቢ የሚያጋጥማቸው ተማሪዎች ሊያዝኑ ወይም ሊበሳጩ፣ ከተለመደው የበለጠ አካላቸውን ሊያማቸው፣ ዝቅተኛ ውጤቶች ሊያገኙ ወይም ትምህርታቸውን ሊተዉ ይችላሉ።
የትምህርት ቤት ዲስትሪክቱ ኃላፊነት የሚኖርበት መቼ ነው?
አንድ ዲስትሪክት አድሏዊ ትንኮሳ መኖሩን ሲያውቅ ወይም እየተከሰተ መሆኑን በአሳማኝ ሁኔታ ማወቅ ሲኖርበት ይህን ለመፍታት የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት። አድሏዊ ትንኮሳ የሚፈጸመው በክፍል ውስጥ፣ በመተላለፊያዎች ላይ፣ በእረፍት ጊዜ ወይም በአውቶቡስ ውስጥ ከሆነ እና ይህ በትምህርት ቤት ሰራተኞች ከተረጋገጠ ሰራተኞቹ ትምህርት ቤቱን ውጤታማ በሆነ መልኩ ምላሽ እንዲሰጥ ለማስቻል ይህን ለርዕሰ መምህሩ ሪፖርት ማድረግ አለባቸው።
ዲስትሪክቶች በተጨማሪም በአንድ ተማሪ ወይም የተማሪዎች ቡድን ላይ ጥበቃ የሚደረግለት ምድብን መሰረት ያደረገ ያልታሰበ የአድሏዊነት ውጤት ሊኖራቸው የሚችል ማንኛውንም ፖሊሲዎቻቸውን ማሻሻል አለባቸው።
ይህ አድልዎ ወይም ሌላ ነገር መሆኑን እንዴት አውቃለሁ?
ልጅዎን የሚያጋጥሙት ችግሮች በአድልዎ ወይም ሌላ ምክንያት የተፈጠሩ መሆናቸውን ለይቶ ማወቅ ከባድ ሊሆን ይችላል። ልጅዎ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ምድቦች መካከል በአንዱ ውስጥ የሚመደብ ከሆነ፣ አደገኛ አካባቢ ካጋጠመው እና ትምህርት ቤቱ ችግሩን ካልፈታ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ያስቡ:
- ይህ ችግር እየተፈጠረ እንደሆነ የማስበው ለምንድን ነው?
- ልጄ ይህ ችግር እየተፈጠረ እንደሆነ የሚያስበው ለምንድን ነው?
- የልጄ መምህር ይህ ችግር እየተፈጠረ እንደሆነ የሚያስበው ለምንድን ነው?
- ይህ ችግር ማንኛውም ሌላ ሰው ላይ አጋጥሟል? ለምን?
ልጅዎን አድልዎ እያጋጠመው ከሆነ ይህን ሰራተኞች መመርመርና በአግባቡ ምላሽ መስጠት እንዲችሉ ለማድረግ ለዲስትሪክቱ ያሳውቁ።
ትምህርት ቤቱን ወይም ዲስትሪክቱን ከማነጋገርዎ በፊት ማሰብ ያሉብዎ ነገሮች
- ስለ ክስተቱ በተመለከተ እርስዎ ወይም ልጅዎ የምታስታውሷቸውን እንደ ቀን፣ ሰዓት እና ተሳታፊ ሰዎች የመሳሰሉ ማንኛውንም ነገሮች ይጻፉ። የጽሁፍ ማስታወሻዎን ከትምህርት ቤቱ ወይም ዲስትሪክቱ ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ይዘው ይቅረቡ።
- ይህን ሁኔታ ለመፍታት ልጅዎን ምን እንደሚያስፈልገው እና ትምህርት ቤቱ ምን ማድረግ እንዳለበት ያስቡ። የሚከተለውን ያስቡ:
- የትምህርት ቤቱን ሁኔታ ይህ ባህሪ በልጅዎ ወይም በሌሎች ተማሪዎች ላይ በማይደገምበት ሁኔታ ለመፍታት ምን ለውጦች መደረግ አለባቸው?
- ትምህርት ቤቱን ለሁሉም ሰው ጋባዥ ለማድረግ ሰራተኞች እና/ወይም ሌሎች ተማሪዎች ምን ድጋፎችን ሊያደርጉ ይችላሉ?
- ልጅዎን በትምህርት ቤት ደህንነትና ምቾት እንዲሰማው ምን ያስፈልገዋል? በአንድ ሰው ላይ የሚያጋጥም ክስተትን ብቻ ሳይሆን የትምህርት ቤቱን ሁኔታ ወይም ባህል ስለመፍታት ያስቡ። አንደኛው መሳሪያ ክስ የሚቀርብባቸው ትንኮሳ ፈጻሚዎች በተመሳሳይ የመማሪያ ክፍል ወይም ቦታ ላይ የማይሆኑበት የደህንነት ዕቅድ ሊሆን ይችላል።
- የተማሪዎች የየግል ሥነ ምግባር ተገቢ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ይህ አይነቱ ድርጊት አደገኛ አካባቢው እንዳይኖር አያደርግም ወይም ትኮሳ በድጋሚ እንዳይከሰት አይከላከልም።
ቀጣይ ደረጃዎች
ቤተሰቦች ከትምህርት ቤቱ ወይም ዲስትሪክቱ ጋር ኢ-መደበኛ የመፍትሄ ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ መደበኛ ቅሬታ ስለማስመዝገብ ሊያስቡ ይችላሉ:
መደበኛ ቅሬታዎችን ማስመዝገቢያ አማራጮች
ለትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች
- ቅሬታዎን በቀጥታ ለትምህርት ቤት ዲስትሪክቱ ርዕሰ መምህር ወይም የዲስትሪክቱ የሲቪል መብቶች አስተባባሪ ሊያስመዘግቡ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የትምህርት ቤት ዲስትሪክትዎን ድረገጽ ይጎብኙ።
Washington State Office of the Superintendent of Public Instruction Office of Equity & Civil Rights
- አንዴ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቱ የቅሬታ ማቅረቢያ አማራጮች ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋላ OSPI Office of Equity & Civil Rights አድልዎን፣ አድሏዊ ትንኮሳን እና ወሲባዊ ትንኮሳን የተመለከቱ ቅሬታዎችን ይመለከታል። ለተጨማሪ መረጃ: https://ospi.k12.wa.us/policy-funding/equity-and-civil-rights/complaints-and-concerns-about-discrimination
U.S. Department of Education Office for Civil Rights (OCR, የዩ.ኤስ የትምህርት መምሪያ የሲቪል መብቶች ኦፊሰር)
- OCR በፕሮግራሞች ወይም ተግባሮች ላይ ዘርን፣ ቀለምን፣ ብሄራዊ ማንነትን፣ ጾታን፣ አካል ጉዳተኝነትን እና ዕድሜን መሰረት አድርጎ የሚፈጸም አድልዎን የሚከለክሉ የፌደራል የሲቪል መብቶችን ያስፈጽማል። ለተጨማሪ መረጃ: https://www2.ed.gov/about/offices/list/ocr/index.html
Washington State Human Rights Commission (WSHRC, የዋሽንግተን ግዛት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን)
- WSHRC ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በስራ ቅጥር ላይ እና በህዝብ አገልግሎት ቦታዎች የሚፈጸም አድልዎን የሚከለክለውን Washington Law Against Discrimination (RCW 49.60, የዋሽንግተን የጸረ አድልዎ ሕግን) ያስፈጽማል። ለተጨማሪ መረጃ: https://www.hum.wa.gov/file-complaint
የዩ.እስ የፍትህ መምሪያ (DOJ, U.S. Department of Justice)፣ የትምህርት ዕድሎች ክፍል
- DOJ በህዝብ ትምህርት ቤቶች ዘርን፣ ቀለምን፣ ብሔራዊ ማንነትን፣ ጾታን፣ አካል ጉዳተኝነትን እና ሀይማኖትን መሰረት አድርጎ የሚፈጸም አድልዎን የሚከለክሉትን የፌደራል የሲቪል መብቶች ሕጎች ያስፈጽማል። ለተጨማሪ መረጃ: https://www.justice.gov/crt/educational-opportunities-section
ቅሬታዎች በዝርዝር: ድርጅት እና የሚፈጸሙ ሕጎች/ፖሊሲዎች |
የጽሁፍ ቅሬታ ያስፈልጋል? | ቅሬታ ማስመዝገቢያ የጊዜ ሰሌዳ | የኤጀንሲ ምርመራ/ውሳኔ ማጠናቀቂያ የጊዜ ሰሌዳ |
---|---|---|---|
የትምህርት ቤት ዲስትሪክት የፀረ-አድልዎ ፖሊሲና ሥነ ሥርዓት3 |
አዎ4 | ፖሊሲውን ይመልከቱ፣ ከ1 ዓመት ባላነሰ ጊዜ ውስጥ። ለትምህርት ቤት ቦርድ ይግባኝ ለማለት 10 የካላንደር ቀናት (ወይም ከዋና ተቆጣጣሪ ምንም ምላሽ ካልተገኘ 30 የካላንደር ቀናት) |
ቅሬታው በቀረበ በ30 የካላንደር ቀናት ውስጥ: በዋና ተቆጣጣሪ የሚሰጥ የጽሁፍ ምላሽ። ለትምህርት ቤት ቦርድ ይግባኝ የሚባል ከሆነ: በ20 የካላንደር ቀናት ውስጥ ችሎት ይሰማና በ10 የካላንደር ቀናት ውስጥ የጽሁፍ ውሳኔዎች የሚሰጡ ሆኖ ለ OSPI ይግባኝ የማለት አማራጭን በተመለከተ መረጃ ይሰጣል። |
OSPI – Equity & Civil Rights5 RCW 28A.642.010 WAC 392-190 |
አዎ | በOSPI በአሳማኝ ምክንያት ካልተራዘመ በስተቀር የትምህርት ቤት ቦርዱ ውሳኔ ከደረሰው በኋላ በ20 የካላንደር ቀናት ውስጥ | OSPI “ምርመራ ማድረግ ሊጀምር ይችላል”፤ ምርመራ ለማጠናቀቅ የተቀመጠ ምንም የጊዜ ሰሌዳ የለም። ከምርመራው በኋላ OSPI የጽሁፍ ውሳኔ ይሰጣል። |
Washington State Human Rights Commission (WSHRC, የዋሽንግተን ግዛት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን)6 Washington Law Against Discrimination RCW 49.60 |
አዎ | የአድልዎ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ በ6 ወራት ውስጥ | ስለ ህዝብ አገልግሎት አድልዎ የቅሬታ አሰራሮች የተመለከቱ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት WSHRCን ያነጋግሩ። |
U.S. Dept. of Education Office of Civil Rights (OCR)7 • ርዕስ VI • ርዕስ IX • ርዕስ II: Age Discrimination Act (ዕድሜን መሰረት ያደረገ አድልዎ ህግ) • ክፍል 504: Rehabilitation Act (የማቋቋሚያ ሕግ) • Age Discrimination Act (ዕድሜን መሰረት ያደረገ አድልዎ ህግ) |
አዎ | በአጠቃላይ ጊዜው በአሳማኝ ምክንያት በ OCR ካልተራዘመ በስተቀር አድልዎን የተመለከተ ክስ በቀረበ በ180 የካላንደር ቀናት ውስጥ | OCR ቅሬታዎቹን “በወቅቱ ይመረምር” እና በቅሬታዎች ምርመራ ላይ ማሻሻያ ያደርጋል። ምርመራው ሲጠናቀቅ OCR የጽሁፍ ግኝቶችን ያቀርባል። |
U.S. Department of Justice (DOJ)8 • ርዕስ IV • ርዕስ VI • ርዕስ IX • Age Discrimination Act (ዕድሜን መሰረት ያደረገ አድልዎ ህግ) • ክፍል 504: Rehabilitation Act • Equal Educational Opportunities Act (EEOA,እኩል የትምህርት ዕድሎች ህግ) |
አዎ | አይ | ምንም በግልጽ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የለም። |
1 Equity and Civil Rights Office, Office of Superintendent of Public Instruction (የእኩልነትና የሲቪል መብቶች ቢሮ፣ የህዝብ መመሪያ አሰጣጥ ዋና ተቆጣጣሪ ቢሮ) አድልዎ፣ አድሏዊ ትንኮሳ እና ወሲባዊ ትንኮሳ: የግጭት አፈታት ከሚከተለው የተወሰደ: https://ospi.k12.wa.us/policy-funding/equity-and-civil-rights።
2 ከላይ ይመልከቱ
3 WAC 392-190 (የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች የህገወጥ አድልዎና አድሏዊ ትንኮሳ ክሶችን የሚመረምሩባቸውና የሚፈቱባቸው የቅሬታና ይግባኝ ሥነ ሥርዓቶችን አዘጋጅተው መተግበር አለባቸው።)
4 ዲስትሪክቶች በተጨማሪም ኢ-መደበኛ የቅሬታ ሥነ ሥርዓት ሊያዘጋጁ የሚችሉ ቢሆንም ይህን ኢ-መደበኛ የቅሬታ ሥነ ሥርዓት በሚጠቀሙበት ወቅት ለቅሬታ አቅራቢዎቹ መደበኛ ቅሬታ የማስመዝገብ መብት እንዳላቸው ማሳወቅ አለባቸው። WAC 392-190-065.
5 https://ospi.k12.wa.us/policy-funding/equity-and-civil-rights
6 የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን https://www.hum.wa.gov/file-complaint
7 https://www2.ed.gov/about/offices/list/ocr/index.html
8 የትምህርት ዕድሎች ክፍል https://www.justice.gov/crt/educational-opportunities-section