የትምህርት ቤት ቀሪ መቆጣጠሪያ፣ ከትምህርት ቤት መቅረት እና በትምህርት ገበታ አለመገኘት
“Becca Bill” (ቤካ ቢል) በመባል የሚታወቀው የዋሽንግተን የስቴት ሕግ ዕድሜያቸው በ 8 እና 18 መካከል ያለ ሕፃናት በመደበኛነት ትምህርት ቤት ገብተው መማር እንዳለባቸው ይደነግጋል።ሕጉ ወላጆችን ወይም ሕጋዊ ሞግዚቶችን ልጆቻቸው በመደበኛነት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ስለ መሆናቸው እንዲያረጋግጡ ያስገድዳል።ተማሪዎች በሕዝብ ትምህርት ቤት፣ በግል ትምህርት ቤት ወይም በቤት ውስጥ ትምህርት ቤት ገብተው መማር ይችላሉ።ሕጉ አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከሌለ በቀር ተማሪዎች በትምህርት ቤት ውስጥ፣ ሙሉ ቀን፣ በየቀኑ መገኘት እንዳለባቸው ያስገድዳል።አንድ ተማሪ ያለ በቂ ምክንያት ከትምህርት ቤት ሳይገኝ ቢቀር፣ ተማሪው እንደ “ሆን ብሎ ከትምህርት ገበታ የሚቀር” ተማሪ ተደርጎ ይቆጠራል። አንድ ተማሪ ሆን ብሎ ከትምህርት ገበታ ይቀራል ከተባለ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲህ እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል፦
- ለቤተሰቦች ማስታወቅ፤
- ለምን እንዲህ እንደሆነ ለማወቅ ከቤተሰብ እና ከተማሪው ጋር ተገናኝቶ አብሮ መወያየትና መፍትሔ መፈለግ፣ እና
- የተማሪውን በትምህርት ገበታ የመገኘት ሁኔታን ለማሻሻል እንዲያግዝ የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም።
ይህ ምንም ውጤት ካላስገኘ፣ ተማሪው እና ቤተሰቡ ወደ Community Truancy Board (የማኅበረሰብ ከትምህርት ገበታ ሆን ብሎ መቅረት ችግር አጣሪ ቦርድ) ወይም ወደ ፍርድ ቤት ሊላኩ ይችላሉ።አንድ ተማሪ፣ ከአሳማኝ ምክንያትም ጋር ቢሆን ብዙ ጊዜ ደጋግሞ ከትምህርት ቤት ከቀረ፣ አሁን ላይ ሕጉ ትምህርት ቤቶች ችግሩ ለምን እንደተፈጠረ ለማወቅ እና ተማሪው በመደበኛነት ወደ ትምህርት ገበታው መመለስ እንዲችል የመፍትሔ ዕቅድ ለማዘጋጀት ከወላጆች ጋር እንዲገናኙ ያስገድዳል። ይህ የሆነበት ምክንያት ከትምህርት ቤት ደጋግሞ መቅረት ወይም “ሥር የሰደደ ከትምህርት ቤት የመቅረት አባዜ” ተማሪው ትምህርቱን በሚገባ መከታተል እንዳይችል ስለሚያደርገው ነው።ከዚህ በተጨማሪ ተማሪው ማግኘት የሚያስፈልገውን ድጋፍ እያገኘ እንዳልሆነ ጠቋሚ ምልክት ሊሆን ይችላል።ስለ ከትምህርት ቤት መቅረት ስናወራ፣ “ብዙ” ማለት እንደ “ትንሽ” ሊመስል ይችላል – በወር 2 ቀን ብቻ ከትምህርት ገበታ ላይ አለመገኘት በራሱ ትልቅ ተፅዕኖን ሊፈጥር ይችላል!
ልጅዎን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ላይ በየቀኑ አስቸጋሪ ከሆነብዎት፣ ትምህርት ቤትዎ እንቅፋቱን እንዲያስወግዱ ሊያግዝዎት እና የእርስዎንም ልጅ በየቀኑ፣ ሙሉ ቀን፣ ሰዓቱን አክብሮ በትምህርት ቤት የመገኘት ልማድን እንዲያጎለብት ሊያግዘው ይችላል። አንድ ተማሪ ከትምህርት ገበታው መቅረቱን ከቀጠለ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል እና ወደ መደበኛ የትምህርት ገበታ ላይ የመገኘት ልማድ ለመመለስ ስለሚያግዙ ሐሳቦች ለማወቅ የ OEO ተዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ይመልከቱዋቸው። በትምህርት ገበታ ላይ መገኘት ላይ ስላለ ችግር ተጨማሪ እገዛ ካስፈለግዎት፣ እባክዎ ስልክ ይደውሉ!የእኛን የድር ጣቢያ እዚህ https://oeo.wa.gov/am ላይ ይጎብኙ ወይም 1-866-297-2597 ላይ ይደውሉ።
ሕጉ ትምህርት ቤቶችን ምን ያስገድዳቸዋል?
- ስለ በትምህርት ቤት የትምህርት ገበታ ላይ መገኘት ስለ ተቀመጡት ደንቦች ለወላጆች ማስታወቅ እና ማስታወቂያው እንደደረሳቸው ለማሳየት ፊርማቸውን ማግኘት
- ተማሪ ከትምህርት ቤት በቀረ ቊጥር ለወላጆች ማስታወቅ፣
- ለምን እንደሆነ ለማወቅ ከወላጆች እና ከተማሪው ጋር ተገናኝቶ መነጋገር፣
- በትምህርት ገበታ ላይ የመገኘት ሁኔታን ለማሻሻል የተለያዩ ዘዴዎችን መሞከር፣ እና በአንዳንድ ሁኔታዎች፣
- ተማሪውን እና/ወይም ቤተሰቡን ወደ Community Truancy Board መላክ።
ሕጉ ተማሪዎችን ምን ያስገድዳቸዋል?
- በትምህርት ቤት ውስጥ፣
- በጊዜ ሳያረፍዱ፣
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከሌለ በቀር በየቀኑ።
- What about children younger than 8? Do they have to be in school?
- What about teenagers? Can they leave school before turning 18?
- What is an "excused" or "unexcused" absence?
- Who decides whether an absence is excused?
- What if my child is late to school? Or skips a class?
- What if my child is sick a lot, and can’t make it to school?
- What does missing “a lot” of school mean?
- What will happen if my child misses a lot of school?
- Can I (the parent) get in trouble if my child misses a lot of school?
- Can my child be suspended for missing school or being late to class?
- The school asked me to meet to talk about my child’s absences – how can I prepare for the meeting?
- Should my child attend too?
- What kind of things could the school do to help?
- When can my child be sent to truancy court?
- What happens when a district files a truancy petition?
- What is a Community Engagement Board?
- What can happen if my child has to go to court for truancy?
- What happens if my child misses more school when there is already a truancy case?
- Can a child with an IEP be sent to court for truancy?
- What if I, the parent, have a disability and need accommodations?
- What if I don’t speak or read English well?
- What if my child just doesn’t want to go to school, but is keeping up with work at home?
- What if my child is anxious about school and gets angry, breaks down, or just won’t get out of bed?
- What if my foster child has already missed school from moving around a lot, and will have to miss more for court and other appointments?
- What if we lost our housing and my child misses school while we are trying to find a new place? Can I get help from the school?
- What if I feel school has not been a positive place for my child? Do I have to keep sending my child even they are being bullied, facing discrimination, or constantly getting in trouble?
- How can OEO help?
- Where else can I find help or more information?