ልዩ ትምህርት ምን ማለት ነው?

ልዩ ትምህርት ምን ማለት ነው?

አካል ጉዳተኛነት ምንድነው?

 "አካል ጉዳተኝነት የሰው ልጅ ከሚያጋጥመው ነገሮች አንዱ አካል ነው እና በምንም መልኩ የግለሰቦችን በህብረተሰብ ውስጥ የመሳተፍ ወይም አስተዋፅኦ የማበርከት መብታቸውን አይቀንስም።"

--Individuals with Disabilities Education Act (የአካል ጉዳተኞች ትምህርት አዋጅ)፣ 20 U.S.C. §1400(c)

ሰዎች እና የእኛ ህጎች፣ “አካል ጉዳተኝነትን” የሚገልጹባቸው ብዙ የተለያዩ መንገዶች አሉ።

እንዲሁም በአካል ጉዳት ላይ ብዙ የተለያዩ ባህላዊ አመለካከቶች አሉ፣ እና ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለን ግንዛቤ በጊዜ ሂደት ተቀይሯል። One Out of Five: Disability History and Pride Project (ከአምስቱ አንዱ፦ የአካል ጉዳት ታሪክ እና ክብር ፕሮጀክት) የሚለውን ስለ አካል ጉዳት ታሪክ እና ስለ አካል ጉዳት አዎንታዊ ማንነት ማሳደግ የበለጠ ለማወቅ የሚረዱ ማስረጃዎች ይመልከቱ።

በህዝብ ትምህርት ቤቶች ላሉ ተማሪዎች፣ በሁለቱ የፈደራል ህጎች፦ Individuals with Disabilities Education Act፣ ወይም “IDEA” እና Rehabilitation Act (የማገገሚያ አዋጅ) አንቀፅ 504፣ ወይም “አንቀፅ 504” – ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች መብት እና ጥበቃ ይሰጣሉ። እያንዳንዱ እነዚያ ህጎች ለአካል ጉዳተኛ ህጻናት የተለየ ትርጉም ያካትታሉ።

የ IDEA የአካል ጉዳተኛነት ትርጓሜ

IDEA ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች የ IEP (Individualized Education Program፣ የግለሰብ ትምህርት ፕሮግራም) መብት ይሰጣል። “አካል ጉዳተኛ ልጅ” ብሎ የሚገልጸው እንደ ልጅ የተገመገመ እና፦

  • ከ14ቱ ልዩ ምድቦች ውስጥ በአንዱ ላይ እንደተገለጸው አካል ጉዳት ያለው ሆኖ የተገኘ፣ እና
  • በአካል ጉዳት እና በትምህርቱ ላይ ባለው አሉታዊ ተጽዕኖ ምክንያት፣
  • ልዩ ትምህርት እና ተዛማጅ አገልግሎቶች ያስፈልገዋል።

በዋሽንግተን ግዛት፣ የአካል ጉዳተኞች ምድቦች እና የእያንዳንዱ ልዩ ፍቺ፣ በመንግስታችን መመሪያ፣ በ Washington Administrative Code (የዋሽንግተን የአስተዳደር ኮድ)፣ WAC 392-172A-01035 ላይ ተዘርዝሯል

የሚያጠቃልሉት፦

  • ኦቲዝም
  • ማየት እና መስማት የተሳነው
  • መስማት የተሳነው
  • የእድገት መዘግየት
  • የስሜት/የባህሪ እክል
  • የመስማት ችግር
  • የአእምሮ እክል
  • በርካታ እክሎች
  • የአጥንት ጉዳት
  • ሌሎች የጤና ጉዳቶች
  • የተለየ የመማር ችግር
  • የንግግር ወይም የቋንቋ እክል
  • አሰቃቂ የአንጎል ጉዳት
  • አይነ-ስውርነትን ጨምሮ የእይታ እክሎች

እነዚህ እያንዳንዳቸው ምድቦች በትምህርት ህገ-ደንቦች ውስጥ የራሳቸው የሆነ ልዩ ትርጉም አላቸው። አንድ ልጅ ከእነዚህ ምድቦች ውስጥ በአንዱ ውስጥ የሚገባ የአካል ጉዳት እንዳለው የሚጠራጠሩ ከሆነ ልዩ ትርጓሜዎችን ማንበብ ወይም አንድ ሰው ከእርስዎ ጋር እንዲገመግም መጠየቅ ጥሩ ሀሳብ ነው። ትርጓሜዎቹን በ WAC 392-172A-01035, ላይ፣ በhttps://apps.leg.wa.gov/WAC/default.aspx?cite=392-172A&full=true#392-172A-01035 ማግኘት ይችላሉ።

አንድ ልጅ በ IDEA ውስጥ ከተገለጹት አካል ጉዳቶች አንዱ ካለበት ነገር ግን "ተዛማጅ አገልግሎት" ወይም "እርዳታዎች" ብቻ የሚያስፈልገው ከሆነ እና "ልዩ ትምህርት" ካላስፈለገው ተማሪው ለ IEP ብቁ አይሆንም ነገር ግን የአንቀፅ 504 እቅድ ሊያስፈልገው ይችላል።

የአንቀጽ 504 አካል ጉዳት ትርጓሜ

አንቀጽ 504 የትምህርት ዲስትሪክቶች በአካል ጉዳተኞች ላይ አድልዎ እንዳይፈጽሙ ይከለክላል። ተማሪው እኩል ትምህርት ለማግኘት የሚያስፈልገውን ልዩ ትምህርት፣ እርዳታ፣ አገልግሎቶችን ወይም ድጋፎችን እንዲሰጡ ዲስትሪክቶችን ያዛል። የአካል ጉዳተኛ ተማሪን የሚከተሉት እንዳለበት ተማሪ ይገልጻል፦

  • የአካል ወይም የአእምሮ እክል
  • በተጨባጭ የሚገድቡ
  • አንድን ወይም ዋና ዋና የህይወት እንቅስቃሴዎች

ስለ አንቀፅ 504 ተጨማሪ መረጃ ከ U.S. Department of Education (የአሜሪካ የትምህርት ክፍል) Office for Civil Rights (OCR፣ የሲቪል መብቶች ቢሮ) ድህረ ገጽ በተለጠፉት FAQs ላይ፣ እዚህ፦ https://www2.ed.gov/about/offices/list/ocr/504faq.html ፣ ማግኘት ይችላሉ።

እንዲሁም OCR “በ 1973 Rehabilitation Act (የማገገሚያ አዋጅ) አንቀፅ 504 ስር ድብቅ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የሲቪል መብቶችን” https://www2.ed.gov/about/offices/list/ocr/docs/hq5269.html  የሚመለከት በ ቀጥታ መስመር ላይ የሚገኝ መረጃ አለው።  ለሌሎች በቀላሉ የማይታዩ ነገር ግን የተማሪው ትምህርት ላይ ተፅዕኖ ሊያመጡ የሚችሉ የተለያዩ ሁኔታዎችን ይዘረዝራል።

በ IDEA እና አንቀፅ 504 መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?

Diagram of three concentric circles.  The largest circle represents all students.  Within it is a smaller circle representing 504 eligible students.  Within that is the smallest circle representing IDEA eligible students.

በሁለቱም ህጎች ስር፣ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች FAPE ተብሎ የሚጠራ Free Appropriate Public Education (ነፃ ተገቢ የህዝብ ትምህርት) እንዲሰጡ ይጠበቅባቸዋል።  ይህም ማለት ዲስትሪክቶች በአካል ጉዳት ምክንያት በትምህርት ቤት ስኬታማ የመሆን ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች የግል ፍላጎቶች ለማሟላት የተለያዩ አገልግሎቶችን የመስጠት ግዴታ አለባቸው።

አንቀጽ 504 ከ IDEA ይልቅ “ስለአካል ጉዳት” ሰፋ ያለ ፍቺ ያለው በመሆኑ ምክንያት ለብዙ የተማሪዎች ቡድን አገልግሎት ይሰጣል።  ስለዚህ፣ አንድ ተማሪ ለ IDEA የብቁነት መስፈርቶችን ካሟላ እና ለ IEP ብቁ ከሆነ፣ ተማሪው በአንቀፅ 504 እንዲሁ የተጠበቀ ነው። ነገር ግን፣ በአንቀፅ 504 የሚጠበቁ እና የአንቀፅ 504 እቅድ ያላቸው፣ ነገር ግን ልዩ ትምህርት የማያስፈልጋቸው እና በ IDEA ስር ለ IEP ብቁ ያልሆኑ ብዙ ተማሪዎች አሉ። 

ሁለቱ ህጎችያላቸውን ግንኙነት ለማሰብ አንዱ መንገድ ሁሉንም ተማሪዎች ማሰብ ነው፦ በመጀመሪያ፣ ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ አካል ጉዳተኞች (አንቀፅ 504) ናቸው፤ በቁጥር አነስተኛ የሆኑት ደግሞ የአካል ጉዳተኞች እና ልዩ ትምህርት (IDEA) የሚያስፈልጋቸው ናቸው።

ከላይ ያለው በትልቅ ክብ ያለው ምስል ሁሉንም ተማሪዎች ይወክላል። በትልቁ ክብ ውስጥ ያለው መካከለኛ መጠን ያለው ክብ ደግሞ አካል ጉዳተኛ እና ለአንቀፅ 504 አገልግሎት ብቁ የሆኑትን ተማሪዎች ይወክላል።  በቡድኑ ውስጥ፣ አነስተኛው ቡድን እንዲሁ በ IDEA ለሚሰጠው አገልግሎት ብቁ ናቸው። በዚህ ግራፍ ልናስታውስ የሚገባን ቁልፍ ነገር በትንሹ ክብ ውስጥ ያሉት ሁሉም ተማሪዎች፦ የትልቁ ቡድን አካል ናቸው። በተጨማሪም በአካል ጉዳት ምክንያት ከሚደርስባቸው አድሎ በመጠበቅ፣ በትምህርት ቤት ለመሳተፍ የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎቶች ማግኘትን ጨምሮ ሁሉም እንደ ሁሉም ተማሪዎች ተመሳሳይ መብቶች አሏቸው።

በአንቀፅ 504 የተጠበቁ እና ለ IEP ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በአጠቃላይ IEP ብቻ ይኖራቸዋል። በ 504 እቅድ ያሉ ሁሉም ነገሮች በ IEP፣ የእርዳታ ገጾች ላይ በብዛት ወይም በተዛማጅ ዝርዝር ወይም ተጨማሪ አገልግሎት ወይም ድጋፎች ውስጥ ሊካተቱ ይገባል።

ለ IEP ብቁ የሆነ ማንኛውም ህጻን እንዲሁ በአንቀፅ 504 የተጠበቀ ነው። ይህ ለምን ይጠቅማል?

አንቀፅ 504 በ ተማሪዎች ላይ በአካል ጉዳት ምክንያት የሚደርስ አድሎን ይከላከላል። መድልዎ ሊከሰት የሚችለው በፕሮግራሙ ብቁ የሆኑ የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎችን ሲያገለል ወይም ተማሪው በእሱ ወይም በእሷ አካል ጉዳተኝነት ምክንያት ጥቃት ሲደርስበት ወይም ሲደርስባት እና ዲስትሪክቱ ለደረሰው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ምክንያታዊ እርምጃዎችን ካልወሰደ ነው።

ዲስትሪክቱ ሰውን በአካል ጉዳቱ ምክንያት እንዳገለለ ካመኑ፣ ስለ መደበኛ ቅሬታዎች ተጨማሪ የመረጃ አማራጮች በእኛ የ Discrimination መድልዎ ገጽ ላይ ያግኙ።